ምክር ቤቱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቇል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡ የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ሲሆኑ የረቂቅ አዋጁን መሻሻል አስፈላጊነት እና በምርመራው ሂደት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡ የአርሶና አርብቶ አደሩን እና ከፊል አርብቶ […]