ምክር ቤቱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቇል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡ የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ሲሆኑ የረቂቅ አዋጁን መሻሻል አስፈላጊነት እና በምርመራው ሂደት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡ የአርሶና አርብቶ አደሩን እና ከፊል አርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ አገሪቱ ከደረሰችበት ዘርፈ ብዙ እድገት ጋር እኩል ለማራመድ እንዲቻል፣ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማደራጀትና ለተጠቃሚው በአግባቡ ለማሰራጨት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር መንግስት እና የመሬት ተጠቃሚዎች አስተማማኝ የሆነ መረጃ የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የተፈጥሮ ሃብቶችን በዘላቂነት በመጠበቅና በማልማት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ማረጋገጥና አካታች ስርዓት መደንገግ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አድርጎ አፅድቆታል፡፡ በአዋጁ አዲስ ከተካተቱ ጉዳዬች ውስጥ ፦ 1. የገጠር መሬትን መሸጥ መግዛት፣ የወል መሬት በህገ ወጥ መንገድ ወሮ መያዝ እስከ አምስት አመት በእስራት ይስቀጣል። 2. የቀድሞ ትዳራቸዉን በፍቺ አጠናቅቀዉ ዳግመኛ ትዳር የሚመሰርቱ የመሬት ባለቤት የሆኑ ገበሬዎች በትዳር ዘመናቸዉ የነበሩ ሴቶች እንደየወቅታዊ ሁኔታዉ 2. ገበሬዎች አዲስ ከሚመሰርቱት እና ቀድሞ በሚኖራቸዉ የትዳር ህይወት የሴቶችን መብት በሚያስጠብቅ መልኩ የመሬት ባለቤቱ ድርሻዉን ዳግም የይዞታ ምዝገባ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ደንግጓል። በዚሁ አዋጅ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ ባህላዊ የመሬት አጠቃቀምና አያያዝ ህጎችና የግጭት አፈታት ስርዓቶች መሰረታዊ የሆኑ ህገመንግስታዊ መብትቶችን ፣ የሴቶችን መብት እና በሌሎች ህጎች የተሰጡ መብቶች እና ግዴታዎችን የሚጻረሩ ከሆነ ተፈጻሚነት እንደሌላቸዉም ተደንግጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *